የሀዲያ ሚዲያ ኔትወርክ (HMN) ቡድን አባላት ከኦ ኤም ኤን (OMN) ዋና አዘጋጅ አቶ ደጀኔ ጉተማ ጋር ተወያዩ

HMN First Metting w OMN 1

የሀዲያ ሚዲያ ኔትወርክ ቡድን አባላት የኦሮሚያ ሚዲያ ኔትወርክ ኦ ኤም ኤን ዋና አዘጋጅ ከሆኑት ከአቶ ደጀኔ ጉተማ ጋር ፍሬያማ ውይይት አድርገዋል፡፡

የሀዲያ ሚዲያ ኔትወርክ ከኦሮሚያ ሚዲያ ኔት ወርክ ጋር በመተባበር ሀዲያ በሳምንት አንድ በቋንቋው ስለራሱ ጉዳይ ፕሮግራም የሚያስተላልፍበት ሁኔታ ዙሪያ ነው ውይይቱ በዋናነት ያተኮረው፡፡

አቶ ደጀኔ ኦ ኤም ኤን ስኬታማ ሊሆን የቻለበትን ሚስጥር ለሀዲያ ሚዲያ ኔትወርክ አባላት አካፍለዋል፡፡ ኦ ኤም ኤን የተለያዩ ውስጣዊና ዉጫዊ ጫናዎችን በመቋቋም የኦሮሞ ህዝብ ድምጽ ከመሆን አልፎ የመላው ጭቁን ብሄሮች ድምጽ መሆን የቻለው ህዝባዊ ዓላማ አንግቦ በመነሳቱ ነው ብለዋል፡፡

ሀዲያ ሚዲያ ኔት ወርክም ከየትኛውም የፖለቲካ ፓርቲ እና የሀይማኖት ጫናዎች ራሱን ነጻ በማድረግ የሀዲያ ህዝብ ከጥቅምና ክብር ማዕከል አድርጎ ከተንቀሳቀሰ ስኬታማ ይሆናል ብለዋል፡፡

ኦ ኤም ኤን አቅም በፈቀደው ልክ ለHMN አስፈላጊውን ትብብር እንደሚያደርግም አረጋግጠዋል፡፡

ዘወትር ሰኞ ከምሽቱ 1:00 ሰዓት ላይ የሀዲያ ፕሮግራም በኦ ኤም ኤን ለማቅረብ ከስምምነት ተደርሷል፡፡

የHMN ቡድን አባላትም ኦ ኤም ኤን ለሀዲያ ህዝብ የአየር ሰዓት በመፍቀዱ ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡ ከአቶ ደጀኔ ጋር በነበራቸው ውይይት ለወደፊት ስንቅ የሚሆን ነገር ማግኘታቸውን ተናግረዋል፡፡

Leave a comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

One thought on “የሀዲያ ሚዲያ ኔትወርክ (HMN) ቡድን አባላት ከኦ ኤም ኤን (OMN) ዋና አዘጋጅ አቶ ደጀኔ ጉተማ ጋር ተወያዩ”